Announcement በከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ የፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የተግባር ተኮር ልምምድ ስልጠና ተካሄደ

በከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ የፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የተግባር ተኮር ልምምድ ስልጠና ተካሄደ

01st July, 2025

ሰኔ 20/ 2017 ዓ.ም የትምህርት ስልጠና ጥራት ለማስጠበቅ የአሰልጣኞችን ክህሎት ክፍተት መሰረት ያደረገ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ስልጠና በሥራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ኮሌጆች ለመጡ አሰልጣኞች በከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ የፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ ፕሮጀክቱን በቀረጹ አሰልጣኞች የፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና የንድፈ ሀሳብ እና ተግባር ስልጠና በኮሌጁ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የዚሁ ስልጠና አካል የሆነዉ የተግባር ስልጠና በካምፓኒ ዉሰጥ የሚደረገዉን በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በ Animal production ንዑሰ ስልጠና ዘርፍ  በንብ ማነብ  ዙሪያ በምርምር  ማዕከሉ ባለሙያዎች የተግባር ተኮር ስልጠና ለአሰልጣኞቹ ተሰጥቷል፡፡ የከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ ተጠሪ የሆኑት አቶ ጀማል ገዳ የዚህ ፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና የአሰልጣኞችን አቅም በመገንባት በተጨማሪ  እንደ ኮሌጅ በንብ ማነብ የተጀመረዉን ስራ በማጠናከር የንብ ፋርምን በተሻለ መልክ ለማደራጀት የሚያሰችል ልምድ የተቀሰመበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡በከተማ ግብርና ስልጠና ዘርፍ የ Animal production ሴክሽን ሄድ የሆኑት አሠልጣኝ ግርማ ታደሰ የዚህ ፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና የአሰልጣኞችን አቅም በመገንባት  የትምህርትና ስልጠና ጥራትን  ለማስጠበቅ እና ለሰልጣኞች የምንሰጠዉንም ስልጠና ዉጤታማ ከማድረግ ባሻገር በምርምር ማዕከሉ መስክ ላይ ማለትም በንብ መንጋ አያያዝ ሂደት፤ማራብያ እና በላብራቶሪ ዉሰጥ የማር ጥራት መመርመርያ ተግባራቶች ላይ በተግባር ማየታችን ተሞክሮዉን  በኮሌጃችን  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with