፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ሰኔ 27/2017 ዓ.ም ለኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተስፋ ካምፓስ ም/ዲን አቶ ኪሮስ ገ /እግዚአብሔር ያቀረቡ ሲሆን በበጀት አመቱ ውስጥ በዕቅድ ታቅደው እና ከዕቅድ ውጭ የተሰሩቱን ያካተተ ሪፖርት አቅርበዋል ። ኮሌጁ ማሳካት ያለበትን ተልዕኮ ፤ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ምቹ ስልጠና አከባቢን በመፍጠር ፣የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎትን በሚፈለገው ልክ በማስኬድ ከዚህም ጋር ተያይዞ ብቁ ተወዳዳሪ እና የፈጠራ ክህሎቱ ያለው የሰለጠነ የሰው ሃይል ከማፍራት በተጨማሪም የከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ራዕይ ለማሳካት የድርሻችን ከመወጣት አኳያ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በሪፖርቱ ቀርቦ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል ። በዘንድሮው በጀት ዓመት ጥሩ ውጤት እንድናመጣ ከላይ እስከ ታች የግቢው ማህበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ የተወጣ ሲሆን ሰልጣኞች ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ የያዝነውን ግብ ማሳካት ችለናል ሲሉ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልጸዋል ። አያይዘውም የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፣የሪፎርም ስራዎችን ስራን ቆጥሮ ከመስጠትና ከመቀበል ፣የተለያዩ ዕቅዶችን አቅዶ ወደ ስራ ከመግባት፣ ብልሹ አሰራርን በመለየት ማክሰም መቻሉ እና የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እና በትስስር መስራት መቻላችን እንዲሁም የውጭ ድርጅቶች ያሳተፈ ስራ መሠራቱ ኮሌጃችን በዘርፈ ብዙ ተግባራት ግንባር ቀደም እንዲሆን ማስቻሉን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ። በመጨረሻም የቀጣይ በጀት አመት እቅድ ፣ በጎ ፈቃድ ተግባራት እና የ90 ቀን እቅድ አተገባበር ላይ ትኩረት ሰጥተን በትጋት ልንሰራ ይገባል በማለት አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡






.