Announcement የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

13th July, 2026

ሀምሌ 1/11/2018
​የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በስኬት ገመገመ።
​ሪፖርቱን ያቀረቡት የኮሌጁ ዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ከበደች አስራት ሲሆኑ፣ በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ የታዩ ጠንካራ የሥራ አፈጻጸሞችን በዝርዝር ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።
​የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ በበኩላቸው፤ የቀረበው ሪፖርት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው፣ በኮሌጁ የተሠሩ የበጎ አድራጎትና የኢኒሼቲቭ ሥራዎችን በማጎልበት ረገድ የታዩ ስኬቶችን አጉልተዋል። በተጨማሪም ስልጠናውን ከአቅርቦት መር ወደ ፍላጎት መር (Demand-driven) ሥርዓት በመቀየር፣ በመደበኛና በአጫጭር ሥልጠናዎች የተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች በሪፖርቱ መካተታቸውን አስገንዝበዋል።
​በመጨረሻም፣ የአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት ያለበትን ደረጃና በቀጣይ በትኩረት የሚተገበሩ ዋና ዋና ሥራዎችን አስመልክቶ የኮሌጁ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ማሞ ኃይሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
​ኮሌጁ የተጀመሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማስቀጠል በቀጣይም የሥልጠና ጥራቱንና ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን በግምገማ መድረኩ ላይ ተመላክቷል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with