የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት የወተት ተዋፅኦ የተግባር ስልጠና መስጫ ወርክ ሾፕ ተደራጀ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም
በዛሬው እለት በአቃቂ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት በተሟላ መልኩ የወተት ተዎፅኦ የተግባር ስልጠና መስጠት የሚያስችለውን ክፍል በልዩ ሁኔታ ለስልጠና ምቹ እንዲሆን በማደስ እና የስልጠና ግብአቶችን በበቂ ሁኔታ በማሟላት በይፋ ማስጀመሩን አበሰረ። የስልጠና ክፍሉ የላብራቶሪ ቴስት ማሽነሪዎችን በመያዙ የወተት ጤናማነት ማረጋገጥ በሚያስችል አቅም ማደራጀቱን አሰልጣኝ ታደሰ ገልፀዋል ።
የሰልጣኞችን ትምህርት በተግባር የተደገፈ በማድረግ ውጤታማ ስልጠና በመስጠት የበቁ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማ ፍራት አወንታዊ ሚና እንዳለው የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በዚህ መልኩ ለማደራጀት እገዛ ያደረጉትን የኮሌጁ አመራሮች እና EASE project አስተባባሪዎች እንዲሁም ሰልጣኞችንም አመስግነዋል ።




.