Announcement በመንግስት ግዥ የህግ ማእቀፍ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

በመንግስት ግዥ የህግ ማእቀፍ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

24th July, 2025

በአቃቂ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በመንግስት ግዥ የህግ ማእቀፍ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም 
በዕለቱም የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉ /ም/ ዲን  አቶ ማሞ ኃይሉ ሲሆኑ ስልጠናው የተዘጋጀበት አላማ በኮሌጁ የመንግስት ግዥ የህግ ማእቀፍ ዙሪያ ያሉ መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ እና ሰራተኞች የግዥ አዋጅን፣መመሪያን የተከተለ አሰራር ስርዓት ተከተለው የመፈጸም እና የማስፈጸም  አቅምን  ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አሳስበዋል ። በመቀጠልም በእለቱ ስልጠና የሰጡት  አቶ ደሳለኝ አደም የመንግስት ግዥ አፈጻጸም  ስርዓቱን  ለማካሄድ  የግዥ መርሆችን ፣የህግ ማእቀፎችን የተከተለ ቀልጣፋና ውጤታማ የግዥ አፈጻጸም  ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል ሂደቶችን ግልጽ በሆነ መንገዲ ግንዛቤ ፈጥረዋል ። በተለይ ከግዥ ፍላጎት እስከ ጨረታ አወጣጥ እና የጨረታ ተወዳዳሪ መብትና ግዴታዎችን የያዘ አዋጅን  መመሪያን መሠረት ተደርጎ መሠራት እንዳለበት በስልጠናው ግንዛቤ ተፈጥሯል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with