Announcement የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰርቬይንግ ዲፓርትመንት የሰልጣኞችሞደል COC የኦንላይን (Online) ፈተና በዛሬው ዕለት ሰጠ።

የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰርቬይንግ ዲፓርትመንት የሰልጣኞችሞደል COC የኦንላይን (Online) ፈተና በዛሬው ዕለት ሰጠ።

13th July, 2026

ሀምሌ 3/11/2018
የዲፓርትመንቱ ሀላፊ አሰልጣኝ ዓላዛር ተሾመ እንደገለጹት ይህ ፈተና የተዘጋጀው በኮሌጁ ስልጣናቸውን አጠናቀው ለሚመረቁ ሲሆን ሰልጣኞች ወቅታዊ የሙያ እና የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ለመመዘን እንዲሁም ክፍተቶችን በመለየት ቀጣይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት ታስቦ መሆኑን  ገልጸዋል።

ፈተናው በዘመናዊ የኦንላይን መፈተኛ ዘዴ (Online Testing System) አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን፥ ይህም ኮሌጁ የጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ጉዞና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተግባር ያሳየበት ሆኗል።

የኮሌጁ ስልጠናና አካዳሚ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ፋንታዬ እንደገለፁት ይህ CoC የሞደለ ፈተና ጥራቱን የጠበቀና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሆነ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ፥ የሰርቬይንግ ዲፓርትመንት ይህንን የኦንላይን ምዘና በማዘጋጀት ላሳየው ተነሳሽነትና ውጤታማ ስራ ምስጋና አቅርቧል። በቀጣይም መሰል የዲጂታል አሰራሮችን በሌሎች ክፍሎችም ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
“በቴክኖሎጂ የታገዘ የክህሎት ልማት ለተቋማዊ እድገት!”

.

Copyright © All rights reserved.

Created with