የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሔደ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ነሃሴ 12/2017 ዓ.ም
ወርቃማ ሰኞ ላይ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ልምድ አካፈሉ ።
ልምዳቸውን ባካፈሉበት ወቅት ለነገሮች ልዩ ትኩረት በመስጠት ተልዕኮን ለማሳካት ጥረት ማድረግ አሁን ላሉበት ደረጃ ለመድረሳቸው እንደጠቀማቸው እና የተቸገሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከተረፈን ላይ ሳይሆን ከሌለን ነገር ላይ ማገዝ እና በተግባር መኖር ትልቅ የአእምሮ ሰላም እንዳለው በተግባር ያሳለፉትን ልምድ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ አካፍለዋል ። አያይዘውም ከህይወት ልምዳቸው በመነሳት ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ልናሳካ ያሰብናቸውን የህይወት ግቦች እንድናሳካ በታማኝነት ተግተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል ።
.