በጋርመንት ስልጠና ክፍል ለደረጃ ሦስት መደበኛ ሰልጣኞች ምዘና ተሰጠ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀምሌ 10/ 2017 ዓ.ም
በጋርመንት ስልጠና ክፍል ለደረጃ ሦስት መደበኛ ሰልጣኞች ምዘና መሠጠቱን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጋርመንት ስልጠና ክፍል ተጠሪ የሆኑት ወ/ሮ የውብነሽ ገለፁ። አያይዘውም ይህ የተቋም ምዘና ዋና ዓለማው ሰልጣኞች ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ከመሸጋገራቸው በፊት ለክህሎት መለኪያ የሚደረግ ሲሆን ሰልጣኞች በቀጣይ የተሻለ
እውቀት እንዲኖራቸው እና የክህሎት ክፍተታቸውን (Skill Gap) ማወቅ፣ ለአገር አቀፍ ስልጠና ማዘጋጀት እንዲሁም የስልጠና ጥራትን ማሻሻል ዋና ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በእለቱም ይህ የተቋም ምዘና በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ አሰልጣኞች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል ።



.