ሰኔ 25/2017ዓ.ም የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ዲኖች ፣ ዲፓርትመንቶች ፣ዳይሬክተሮች እና ምዝገባውን የሚያስተባብሩ የ ICT Department አሰልጣኞች በተገኙበት የ E-Schooling ምዝገባ ያለበት ደረጃ ተገመገመ ። ለግምገማው መነሻ የሚሆን አስልጣኝ ይነበብ ታምሩ እና አሰልጣኝ ደጀኔ ቶላ ሪፖርት አቅርበው ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ተነስቶ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ። እስከ አሁን ያለው የምዝገባ ሂዴት የተሻለ እንቅስቃሴ እንዳለው ገልጸው በቀጣይ ቀናት የኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ በሚወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ለመዝገበ እንደሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ። አያይዘውም ለስራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት በምሽት መርሃ ግብር የሚሠራ መሆኑን ገልፀዋል ። ሰራተኞች ፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ሰልጣኞች መረጃቸውን ከሰኔ 30 በፊት ሞልተው እንዲጨርሱ አቶ ፀጋዬ አዱኛ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።


.