Announcement አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገመገመ

አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገመገመ

13th July, 2026

አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገመገመ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀምሌ/2018 ዓ.ም

​የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ክንዋኔ የፕሮጀክቱን የስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ፕላን መነሻ በማድረግ ከፕሮጀክቱ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በስፋት የገመገመበት መድረክ አካሄደ።

​ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ በመድረኩ መግቢያ ላይ እንደገለጹት፤ የEASE ፕሮጀክት በ2018 በበጀት ዓመት የEASE 2ተኛ አመት የስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ፕላንን መሠረት በማድረግ በ3 ዲፓርትመንቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሠራ መቆየቱን ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ በአውቶሞቲቭ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ፣ጋርመንትና ሌዘር ዲፓርትመንቶች የሥልጠና ግብዓቶችን ከማሟላት ጀምሮ የሥልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

​በመቀጠልም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ጫላ ገለቴ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን እና የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚያሳይ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተጫማሪም በአቃቂ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኢዝ ድጋፍ በስራና ክህሎት አስተባባሪነት የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን በማሳተፍ የተዘጋጀው  የኢቪ (EV - Electric Vehicle) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የሙያ ደረጃ /OS/ ማሻሻል ፣የካሪኩሉም ቀረጻ እና ከደረጃ 3-እስከ ደረጃ 5 የማስተማሪያ ሞጁል ተዘጋጅቶ ለእውቅና/Validation ቀርቧል::

​   በቀረበው ሪፖርት እና በኢቪ (EV - Electric Vehicle) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ የተሰሩትን ስራዎች ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር (MOLS) ፣ የኮሌጁ ከኢንዱስትሪ አድቫይዘሮች ቦርድ አባላት፣የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከር በቀጣይ በጀት አመት ፕሮጀክቱ ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ያሏቸውን ሃሳቦች በማስቀምጥ ተጠናቋል፡ ፦

.

Copyright © All rights reserved.

Created with