መልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራርን መለየት እና ማክሰም ላይ ስልጠና ተሰጠ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ነሃሴ 3 / 2017 ዓ.ም
ለአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና አስተባባሪዎች የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራርን መለየት እና ማክሰም ላይ ስልጠና ተሰጣቸው ።
ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽሕፈት ቤት የመልካም አስተዳደር ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ወረታ ሲሆኑ በስልጠናውም :-
👉 የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራር ፅንሰ ሃሳብ
👉የመልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ
👉የመልካም አስተዳደር መገለጫዎች በአለም አቀፍ ተቋማት የተሰጠው ትርጉም
👉የመልካም አስተዳደር መርሆች
👉የመልካም አስተዳደር የማስፈን ሂደት ላይ የተለያዩ አካላት ሚና
👉 በቅሬታ እና አቤቱታ አፈታት
👉የመልካም አስተዳደር አሰራር መለያ መስፈርቶች በሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቀረቡት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ሃሳብ አስተያየት የሰጡ ሲሆን አቶ ተስፋዬ ወረታ ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዘውም ዜጐች ለሚያነሱት ጥያቄ ፈጣንና ተገቢ ምላሽ በመስጠት መልካም አስተዳደርን በማስፈን የተቋሙን አላማ ማሳካት ይገባል ብለዋል።
የተሰጠውን ስልጠና መነሻ በማድረግ በኮሌጆችን ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጥራትና ጥንቃቄ በመለየት በእቅድ ላይ ተመሰረተን በየደረጃው መፍታት እንደሚገባ እና ብልሹ አሰራሮችን በማክሰም ይዘነው የተነሳነውን ራዕይና አላማ በጋራ ተባብረን በማሳካት ሁልግዜም ለውጤት መትጋት እንደሚያስፈልግ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ። በመጨረሻም ስልጠናውን ለሠጡት አሰልጣኝ ምስጋና አቅርበው ስልጠናው ተጠናቋል ።


.