Announcement ለተተኪ ሴት አመራሮችና ለኮር አመራሮች የሴቶች አቅም ማጎልበቻ እና የሥራና ሕይወት ሚዛን ስልጠና ተሰጠ ።

ለተተኪ ሴት አመራሮችና ለኮር አመራሮች የሴቶች አቅም ማጎልበቻ እና የሥራና ሕይወት ሚዛን ስልጠና ተሰጠ ።

13th July, 2026

ሰኔ 27/2018 ዓ.ም
የአመራር ብቃትን ለማሳደግ፣ የሴቶችን ተሳትፎ እና የአመራር ሚና ለማጠናከር እንዲሁም በሥራና በግል ሕይወት መካከል ጤናማ ሚዛን እንዲፈጠር ያለመ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለሴት አመራሮች በተሳካ ሁኔታ መሰጠቱን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ወ/ሮ ይርጋዓለም መሃሪ ገልፀዋል ።
በስልጠናው ላይ ከተለያዩ ኮሌጃች የተውጣጡ ሴት ዲኖችና የኮሌጁ ሴት አመራሮች እና ተተኪ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በስልጠናውም የአመራር ክህሎታቸውን፣ የውሳኔ አሰጣጥ ብቃታቸውን፣ የተግባቦት እና የቡድን አመራር ችሎታቸውን የሚያጠናክሩ ርዕሶች በሰፊው ቀርበዋል።
በተጨማሪም የሴቶች አመራር ተሳትፎን የሚያጎለብቱ አስተያየቶችና የሥራና የቤተሰብ ኃላፊነትን በሚዛናዊ ሁኔታ ለማስተዳደር የሚያግዙ ልምዶች ተካፍለዋል።
በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ማሞ ሃይሉ እንደገለፁት ሴቶችን በአመራር ዘርፍ ማብቃት የተቋማትን ውጤታማነት፣ የሠራተኞችን ተነሳሽነት እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ተሳታፊዎችም በሥራ ቦታቸው አርአያ በመሆን ሌሎችን የሚያበረታቱና የሚመሩ አመራሮች እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ስልጠናው በቡድን ውይይት፣ በተግባራዊ ልምምዶች እና በልምድ ልውውጥ በመታገዝ ተሳታፊዎች በሥራ ቦታ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍታት የሚችሉበትን አቅም አጎልብቷል።
በማጠቃለያው ተሳታፊዎች ከስልጠናው ያገኙት እውቀትና ክህሎት በሥራ ቦታቸው በተግባር እንደሚያውሉት በመግለጽ የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ተሳትፎ ያለው አመራር ለማጠናከር እና ጤናማ የሥራና ሕይወት ሚዛን ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን እንዲኖራቸው ዶ/ር ተመስገን ስልጠናውን ሰጥተዋል ።
በመጨረሻም እንዲህ አይነት ስልጠናዎች የሴቶችን የአመራር አቅም ለማጎልበት እና ተቋሙ ብቁ፣ ተሳታፊ እና ውጤታማ አመራር ለመፍጠር ስለሚያግዝ ሌሎች ተመሳሳይ ስልጠናዎች በቀጣይነት እንደሚያካሂዱ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ በማጠቃለያ ንግግራቸው ገልፀዋል ፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with