የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና GIZ-QEP II አጋርነት፡ የሰልጣኞች የውስጥ ቢዝነስ ፕላን ውድድር ተካሄደ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀምሌ /2018ዓ.ም
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGIZ-QEP II ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ላለፉት 6 ወራት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች ያሳተፈ የውስጥ ቢዝነስ ፕላን (Business Plan) ውድድር አካሄደ።
በውድድሩ መክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ የGIZ-QEP II ተወካይ ወ/ሪት ጊዜወርቅ እና የቡድኑ አባላት በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ወ/ሪት ጊዜወርቅ፥ ይህ የቢዝነስ ፕላን ውድድር ሰልጣኞች ወደ ስራው ዓለም ከመግባታቸው በፊት አቅማቸውንና የፈጠራ ስራቸውን የሚያሳዩበት እጅግ ወሳኝ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም በውድድሩ ላይ ተሳትፈው በቀጣይ የተሻለ እና አዋጭ የቢዝነስ ፕላን ይዘው ለሚቀርቡ ለስድስት (6) ቡድኖች ድርጅታቸው (GIZ-QEP II) የመነሻ ካፒታል የሚያመቻች መሆኑን በይፋ አብስረዋል።
ይህ ውድድር ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባራዊ የንግድ ሃሳብ በመቀየር ራሳቸውንና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ስራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ሆኗል።
አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የእውቀት እና የተግባር ክህሎት መገኛ!
.