Announcement በእውቀት ላይ የተመሰረተ እቅድ ለተቋም ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ አለው ።

በእውቀት ላይ የተመሰረተ እቅድ ለተቋም ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ አለው ።

12th August, 2025

በእውቀት ላይ የተመሰረተ እቅድ ለተቋም ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ አለው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ነሃሴ 5 / 2017 ዓ.ም

ለአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና አስተባባሪዎች የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራርን መለየት እና ማክሰም ላይ ስልጠና ተሰጣቸው ።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ ሲሆኑ በስልጠናውም :-
👉 ምርጥ ተሞክሮ መለያ ፣ መቀመሪያ እና ማስፊያ
👉የተቋም ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ማሳደግ 
👉የከተማ መልካም አስተዳደር ችግር መፍታት፣ የአቤቱታ መወሰንና ማስፈጸም አቅም ማጎልበት እና ተቋማዊ የቅንጅት፣ የትብብርና የድጋፍ አሰራር ስርዓትን ማሻሻል 
👉የዕቅድ/ሪፖርት ዝግጅት፣ የኢንሸቲቭ ስራዎች አሰራር ሥርዓትን ማጎልበት  በሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቀረቡት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ሃሳብ አስተያየት የሰጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። 
ስልጠናው ውስጣችንን በደንብ አይተን በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ እና የሚያተጋ ስለሆነ በቀጣይ ሁሉም የኮሌጅ ማህበረሰብ ሞዴል ተቋም መፍጠር እና ማስቀጠል ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with