ራዕያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን ነው !
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ለማሳካት ውይይት ተካሄደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ለማሳካት ለኮሌጁ ዲኖች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች ፣ እና አስተባባሪዎች በተገኙበት ቀርቦ በሰፊው ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል ።
የውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ሲሆኑ በገለፃቸው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ስድስቱን ግቦች እና
ሃያ አራቱን አላማዎች ለማሳካት ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የባለፈውን አመት ስኬት በተደራጀ እና በተናበበ አግባብ በማስቀጠል ጉድለቶችን ደግሞ በማረም በአንድነት መንፈስ ለውጤት መትጋት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ።
አያይዘውም ለሰራተኞች እና ለስራ ኃላፊዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በእቅዳችን ላይ ተግባብተን ለመስራት በሚያመች መልኩ እየተሠራ መሆኑን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ።
የተቋም ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት በማሳደግ
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ የቅንጅት፣ የትብብርና የድጋፍ አሰራር ስርዓትን ማሻሻል እንደሚገባ
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ም/ዲን አቶ ማሞ ሀይሉ ገልፀዋል ።አያይዘውም ኮሌጁን ለስልጠና ምቹና ሳቢ ለማማድረግ እየተሠራ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ማሞ ሃይሉ ገልፀዋል ።
ለኢንተርፕራይዞች እና ለጥቃቅን አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ድጋፍ በማድረግ ምርትና ምርታማነታቸውን ማሣደግ ላይ ከባለፈው በጀት ዓመት ተሞክሮ በመውሰድ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ወ/ሮ ይርጋዓለም መሃሪ ገልፀዋል ።
አንድ መሪ ስራን በውጤት ለመምራት ከሚመራው ማህበረሰብ ጋር ተግባብቶ የሚሠራውን ስራ እውቆ እና በእቅድ በመመራት አርእያ ሆኖ በመምራት ያሰብነውን ግብ ማሳካት እንደሚቻል የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተስፋ ካምፓስ ም/ዲን አቶ ኪሮስ ገ/እግዚአብሔር ገልፀዋል ።
የዕቅድ/ሪፖርት ዝግጅት፣ የኢንሸቲቭ ስራዎች አሰራር ሥርዓትን ማጎልበት
ከአቅርቦት መር ወደ ፍላጎት መር የስልጠና ሥርዓት በማጠናከር የስልጠና አግባብነትና ጥራትን ማሻሻል ላይ ወጥነት ባለው አግባብ መስራት እንደሚያስፈልግ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ፋንታዬ ባቡሎ ገልጸዋል ።
👉 ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል በማፍራት እና ቀጣይነት ያለው የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ በመስጠት ህብረተሰቡንና ኢንዱስትሪውን በማሳተፍ ምቹ ስልጠና አካባቢ በመፍጠር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በተግባባ ነው አግባብ በየስራ ድርሻው የጎላ ትጋት ሊኖር እንደ ሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል ።

.