የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ኦዲት ፎረም እውቅና አገኘ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሰኔ 27/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ኦዲት ፎረም በተካሄደው የ5 አመት ማጠቃለያ አፈፃፀም ላይ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እውቅና ተሰጥቶታል።
የኮሌጁ የነገሰው ካምፓስ ምክትል ዲን አቶ ገዛኸኝ ደጉ እንደገለጹት በኦዲት ግኝት ላይ ሙሉ በሙሉ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ኮሌጁ ይህንን እውቅና ማግኘቱን ተነግረዋል።
ይህ እውቅና የሚያሳየው ኮሌጁ ቀደም ሲል በኦዲት የተገኙ ድክመቶችን በአግባቡ መፍታት መቻሉን ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኦዲት ፎረም የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን ከብክነት እና ከብልሹ አሰራር ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት መነሻ ባደረገ መልኩ ፈጣን ምላሽ በመስጠትማስተካከል መቻሉን አቶ ገዛኸኝ ደጉ ገልፀዋል ።
.