Announcement በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ

በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ

13th July, 2026

ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
​"ተስፋን እንተከል" በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የኮሌጁ ማህበረሰብ እና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ ሁለት አመራሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።
​አቶ ፀጋዬ አዱኛ የኮሌጁ ዋና ዲን እንደገለፁት
​"ይህ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ኮሌጁ በሀገራዊ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ (Green Economy) እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን አወንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ነው" ብለዋል።
እንዲሁም ​አቶ ማሞ ሀይሉ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን እንደገለጹት "የአረንጓዴ አሻራ የዘመቻ ሥራ ሣይሆን የሁል ጊዜ ተግባራችን መሆን አለበት" ያሉት ም/ዲኑ፤ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ እያንዳንዱ ዜጋ ሊተገብረው የሚገባ ብሔራዊ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል።
​ኮሌጁ መንግሥት እያስቀጠለ ላለው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ሁነኛ አጋር መሆኑን በመግለጽ፣ በዘንድሮው ዓመት 2,510 ለምግብነት ፣ ለጥላና ፣ ለውበት የሚያገለግሉ የተለያዩ የችግኝ ዝርያዎችን መትከል መቻሉን እንድሁም የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ረገድም የተቋሙ ማህበረሰብ የበኩሉን እንደሚወጣ አያይዘው ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with