ሰኔ 30 / 2018 ዓ.ም
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሴቶች ማረሚያና ማረፊያ ማዕከል ጋር በመተባበር ለሴት የህግ ታራሚዎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል። ኮሌጁ አሰልጣኞችን በመመደብ ታራሚዎቹ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎችን አግኝተው የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ እነዚህን መሰል ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ ይቀጥላል። ለስራው መሳካትና ለተገኘው እውቅና አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።