በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰርቨይንግ እና ድራፍቲንግ ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ለሰልጣኞች የተቋም ምዘና ተሰጠ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሐምሌ 10/2017ዓ.ም
ይህ ምዘና በዋነኛነት የተዘጋጀው የሰርቨይንግ ቴክኖሎጂ ( Surveying Technology) ደረጃ ሶስት ሰልጣኞች ሲሆን ይህ የተቋም ምዘና (Institutional Assessment) የሚደረገው ሰልጣኞች ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ከመሸጋገራቸው በፊት የሚደረግ ሲሆን። ይህ የተቋም ምዘና ዋና ዓለማው ለክህሎት መለኪያ የሚደረግ ሲሆን ሰልጣኞች በቀጣይ የተሻለ
እውቀት እንዲኖራቸው እና የክህሎት ክፍተታቸውን (Skill Gap) ማወቅ፣ ለአገር አቀፍ ስልጠና ማዘጋጀት እንዲሁም እና የስልጠና ጥራትን ማሻሻል ዋነኛ ናቸው።
በዛሬው እለትም ይሀ የተቋም ምዘና በተሳካ ሁኔታ እንደተሰጠ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰርቨይንግ እና ድራፍቲንግ ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ አሰልጣኝ አልአዛር ተሾመ ገልፀዋል።በመጨረሻም በእለቱም ይህ የተቋም ምዘና በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ አሰልጣኞች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል ።




.