Announcement መምህራን ማህበር ከጠቅላላ አባላቱ ጋር ጉባኤ አካሄድ

መምህራን ማህበር ከጠቅላላ አባላቱ ጋር ጉባኤ አካሄድ

17th July, 2025

የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሠረታዊ መምህራን ማህበር  ከጠቅላላ አባላቱ ጋር ጉባኤ አካሄድ 
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀምሌ 9/2017ዓ.ም 
 በዕለቱም ጉባኤውን ያስጀመሩት የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ  ሲሆኑ አያይዘውም መሠረታዊ ማህበሩ በኮሌጁ ውስጥ ከጊዜ  ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣ መሆኑን እና በቀጠይም ብዙ ለውጦችን ለማምጣት በሚደረገው የመተካካት ስራ ተቋሙን በሀላፊነት ሊመራ የሚችል መወከል እንዳለባቸው  አሳስበው  አስጀምረዋል በጉባኤው ላይ የ2017ዓ.ም በማህበሩ አመራሮች የተሠሩ የስራ አፈጻጸም እና  በቀጣይ ከ2018 ዓ.ም እስከ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚሰሩ ተግባራት  በዶ.ር ሙሴ ክፍሎም በዝርዝር ቀርቧል። በሪፖርቱ  ከተካተቱ ጠንካራ ጎኖች መካከል  የመጀመሪያው  የመምህራን  ማህበር አመራሮች በየወሩ የሚሰበሰብ  መደበኛ ወርሀዊ መዋጮ ገንዘብ ወደ ከተማ አስተዳደር ፈሠስ መደረጉ፣በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ  በመግባት የነበሩ ቅሬታዎች የድስፕሊን፣ደረጃ እድገት እና የመምህራን ጥቅማ ጥቅም ለማስከበር ጥረት የተደረገ  መሆኑ ተገልጿል ።
በመጨረሻም ከመምህራን  ማህበሩ በተለያዬ ምክንያት የለቀቁ የማህበሩ ተዎካዮችን የማሟላት እና የማህበሩን ስራ አስፈጻሚ  መልሶ የማደራጀት ስራ የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር የአሰልጣኞች ማህበር  ስራ አስፈፃሚ አሰልጣኝ  ዮርዳኖስ አዲስ ባሉበት ምርጫ በማካሄድ  የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሠረታዊ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሴ ክፍሎም ፣አሰልጣኝ ዳዊት አምደ ጺዮን የማህበሩ ፀሀፊ፣ አሰልጣኝ ሚልካ እንድሪያስ የማህበሩ የሴቶች ጉዳይ ፣አሰልጣኝ  ሀና ግረማ የሂሳብ  ሹም፣አሰልጣኝ  እየሩሳሌም ካሳሁን ገንዘብ ያዥ በማድረግ ጉባኤው  ተጠናቋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with