Announcement ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መስራት ውጤት አምጪ እንደሆነ ተገለፀ ።

ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መስራት ውጤት አምጪ እንደሆነ ተገለፀ ።

16th July, 2025

ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መስራት ውጤት አምጪ እንደሆነ ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሐምሌ 8 /2017 ዓ.ም
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 ዕቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሔደ ።
በውይቱ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ ና ክህሎት ቢሮ ባለሙያዎች፣ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ኢንተርፕራዞች፣ የትምህርት ቁጥጥርና ምዘና ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች እና የትምህርት ፅ/ቤት ባለሙያዎች በተገኙበት በኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 እቅድ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ሰፊ የሆነ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል ። 
👉 ህብረተሰቡን እና ኢንዱስትሪውን በማሳተፍ ምቹ የስልጠና አካባቢ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛል
👉 አረንጓዴ አሻራላይ በስፋት እየተሰራ መሆኑ
👉 መደበኛ እና አጫጭር ስልጠናዎች ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ ሆኗል ።
👉አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን ስራ ተሰርቷል
👉 አለም አቀፍ የጥራት ተስማሚነት ደረጃ Iso 9001 ፡ 2015 ሰርቲፋይ መሆን ተችሏል
👉 ካይዘን አተገባበር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሽልማት ማግኘት ተችሏል
👉 የተደራጀ እና የተቀናጀ የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል
👉 ብልሹ አሰራርን ለማጥፋት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል 
👉 ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የስልጠና ቦታ ተፈጥሯል
👉 የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እየተሠራ ይገኛል
👉 የአሰልጣኞች እና አመራሮች ብቃት ለማሳደግ በተለዩ የክህሎት ክፍተቶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል
👉 በሌማት ትሩፋት ላይ ተሞክሮ በመቀመር የማስፋት ስራ እየተሰራ ይገኛል
👉 ምርምር ፈጠራና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሳደግ ስራ ተሰርቷል
ከላይ የተጠቀሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን በማፍራት የኮሌጁን ራዕይ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሠራ መሆኑን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ። አያይዘውም በበጀት ዓመቱ በተሠራው ስራ በርካታ እውቅናዎች እና ሽልማቶች መገኘቱን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም በቀጣይም በትኩረት የሚሰራባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ተብለው የተቀመጡት:-
👉 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ኮሌጅ መጥተው የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ በስፋት መስራት
👉 ተመራቂ ሰልጣኞች ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
👉 አሰልጣኞች 100% ተመዝነው የብቃት ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ማድረግ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ለማሳካት በጋራ ልንሠራ ይገባል ሲሉ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with