Announcement ወረቀት አልባ አገልግሎትን ወደ ተግባር ለማስገባት እንደተቋም በልዩ ተነሳሽነት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

ወረቀት አልባ አገልግሎትን ወደ ተግባር ለማስገባት እንደተቋም በልዩ ተነሳሽነት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

21st July, 2025

ወረቀት አልባ አገልግሎትን ወደ ተግባር ለማስገባት እንደተቋም በልዩ ተነሳሽነት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ90 ቀን እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሐምሌ 11 / 2017 ዓ.ም
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ የዲፓርትመንት ተጠሪዎች በተገኙበት የ90 ቀን እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ ።
በ90 ቀን መሠራት ያለባቸው ተግባራትን እና ያሉበትን ሁኔታ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ አብራርተዋል። 
 በዘጠና ቀን እቅዱ በዋነኝነት በልዩ ትኩረት መሠራት ያለባቸው ተግባራት  ፡ -
👉ኮሌጁን ለስልጠና ምቹ ማድረግ
👉ኢንዱስትሪ አታችመንትን ተግባራዊ ማድረግ 
👉ISO ቀጣይነትን ማረጋገጥ 
👉የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ማከናወን 
👉የስልጠና work-shop ደረጃውን የጠበቁ እንዲሆኑ ማድረግ 
👉ለስልጠናና ለስራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አሰራሩን ጠብቆ ቶሎ እንዲገቡ ማድረግ 
👉ተመራቂ ሰልጣኞች ሀገር አቀፍ ምዘና እንዲወስዱና ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ 
👉መደበኛና አጫጭር ሰልጣኞችን በምዘና ማብቃት 
👉የተለያዩ ቴክሎጂዎችን በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጣችንን ማሻሻል 
👉የንብረት ቆጠራ በተሳካ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ 
👉የBSC ግምገማ በተሳካ መልኩ ማከናወን 
👉የኦዲት ግብረ መልስ (ግኝቶችን) ምላሽ መስጠት 
👉የተጀመሩ የማምረቻ ቴክኖሎጂዎችን ማጠናቀቅ
👉የበጎ አድራጎት ስራዎችን በልዩ ትኩረት ተግባራዊ ማድረግ 
👉የኢንተርፕራይዞችን መረጃ ማጥራት የተቋቋመውን ኢንተርፕራይዝ ወደ ስራ ማስገባት
👉ተመራቂ ሰልጣኞች ወደ ስራ ማስገባት እና ማስተሳሰር
👉12ኛ ክፍል ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ወደ ኮሌጁ መጥተው እንዲሰለጥኑ የተለያዩ የንቅናቄ መድረኮችን መፍጠር የሚሉ ዋና ዋና ተግባራት እና ዝርዝር ሁኔታዎች ተነስተው ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል ።
በዘጠና ቀን እቅድ አፈፃፀም ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ያጋጠሙ ክፍተቶችን በፍጥነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር መፍትሔ መውሰድ እንደሚገባ እና ችግር ፍቺ ክትትልና ድጋፍ በየዘርፉ ሊደረግ እንደሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with