Announcement የተገኘውን የድል ውጤት ለማስቀጠል በኮሌጁ የስራ እንቅፍት

የተገኘውን የድል ውጤት ለማስቀጠል በኮሌጁ የስራ እንቅፍት

12th August, 2025

የተገኘውን የድል ውጤት ለማስቀጠል በኮሌጁ የስራ እንቅፍት የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመለየት ስራ ተሰራ !!!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ነሃሴ 5 / 2017 ዓ.ም
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስራ እንቅፋት የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከዲኖች ፣ ከዳይሬክቶሬቶች ፣ ከዲፖርትመንት ተጠሪዎች ፣ ከቡድን መሪዎች እና አስተባባሪዎች ጋር በመሆን የመለየት እና የማቀድ ስራ ተከናወነ ።
የተለዩ የመልካም አስተዳደርና ችግሮች በስራ ክፍል ፣ በኮሌጁ እና በእናት መስሪያ ቤት መፈታት ያለባቸው ተግባራትን በመለየት የመወያየት እና የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫዎች የማስቀመጥ ተግባር መከናወኑን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል ። አያይዘውም እቅዱን መነሻ ባደረገ መልኩ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ባለቤት በመሆን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳቸውን በመርዳት በእቅድ ተካተው በልዩ ትኩረት ከስር ከስር እየተፈቱ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ማሳካት እንደሚገባ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with